ድጋፍ ያድርጉ
$25 1 አረጋዊ ለ 1 ወር መመገብ ይችላል
ይሳተፉ
የተነሳሽነት እንቅስቃሴዎች
ገንዘብ በማሰባሰብ
የገንዘብ ማሰባሰቢያ ቀን በምናደርግበት ጊዜ ንቂ ተሳታፊ ይሁኑ። ምግብ በማዘጋጀት ፣ ምግብ በመስጠት ፣ ለሽያጭ የሚቀርቡ የእጅ ስራዎችን በማቅረብ ፣ መሳተፍ ይችላሉ። ማንኛውም ልገሳ አረጋውያንን ይደግፋል።
ለጋሽ ድርጅቶችን በማፈላልግ
የእርዳታ ማመልከቻ ልናገኝበት የምንችል ለጋሽ ድርጅቶችን የምታውቁ ከሆነ ጠቁሙን። ወይም የእርዳታ ማመልከቻ የማስገባት ልምድ ካላችሁ እርዱን። በተጨማሪ ገንዘብ የማግኛ መንገዶችን የምታውቁ ከሆነ ፣ ብታስተዋውቁን ድጋፋችሁ ወደብ የሌለው ይሆናል።
ለማገዝ አማራጭ መንገዶች
በማስተዋወቅ
የበጎ ስራ አገልግሎታችን በሁሉም ዘንድ እንዲታወቅ ፣ በማስተዋወቅ አግዙን። ብዙ ሰዎች ካወቁን ፍሬአማዎች እንሆናለን። ታሪካችንን በሶሻል ሚዲያ ለጓደኞቻችሁና ቤተሰቦቻችሁ አስተዋውቁልን።
ቁሳቁስ በመለገስ
አረጋዊያን ይጠቀማሉ የምትሏቸውን ልብሶች ፣ ብርድ ልብሶች ፣ ፎጣዎች ፣ ጫማዎች ለግሱልን። በእርዳታ ማሰባሰቢያ ቀናት እነዚህን እቃዎች ሰብስበን ጎንደር ወደሚገኘው የመረጃ ጣቢያችን በመላክ ፣ ለተረጂዎች እንዲደርስ እናደርጋለን።
ጥያቄዎች?
በጥሬ ገንዘብ ከምትረዱን ሰማንያ በመቶ (80%) በቀጥታ ለምግብና ለምግብ የሚሆኑ እቃዎችን ለመግዛት ይውላሉ። ተቀሪው ሃያ በመቶ (20%) ለስራ ማስኬጃ ይውላል። ይኸውም ለሁለት ምግብ አብሳዮች ደሞዝ ፤ ለአንድ ዘበኛ ደሞዝና ለአንድ የድርጅቱ አስተባባሪ ደሞዝ ይውላል።
የአካባቢው የቀበሌ ማህበር ባዘጋጀው መመዘኛ መስፈርት እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን የመለምሉና ጎንደር ወደሚገኘው ጣቢያችን ይልካሉ ፤ ወይም ስማቸውን ይሰጡናል።
አረጋዊያኑ የሚኖሩት በቤታቸው ሆኖ ለምሳ ወደ ድርጅታችን ይመጣሉ። ሲመጡም ቡና ይፈላላቸውና እርስ በርስ ይጫወታሉ። በመጨረሻም ራታቸውን ቋጥረው ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ። አንድ አረጋዊ መምጣት ካልቻለ የሚአውቀወ ሰው ምሳና እራት እንዲወሰድላቸው መላክ ይችላሉ። የሚውስድላቸው ከሌላቸው ረዳቶችን ወደ ቤታቸው በመላክ ጤንነታቸውን እናጣራና እግረመንገዳችንን ምግቡን እናደርሳለን።
የሙላት ፀጋ አረጋውያን መረጃ ድርጅት በየአመቱ በኢትዮጲያውያን ዘመን መለወጫ ፣ መስከረም አንድ ቀን የእርዳታ ማሰባሰቢያ ባእል ያደርጋል። የተሰበሰበው ገንዘብ ጎንደር ለሚገኙ ድርጅቱን በነጻ ለሚአገለግሉ የቤተሰብ አባሎች ይላካል።