ስለ እኛ
ታሪካችን
እንዃን ወደ ሙላት ፀጋ የአረጋዊያን መረጃ ድርጅት በደህና መጣችሁ። ታሪካችን የሚጀምረው በጎንር ኢትዮጲያ ነው። በዘራችን የተቸገሩ መርዳትን ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ልምድ ነው። በልጀነታችን እያየን ያደግነው ወላጆቻችንና አያቶቻችን ፣ ልባቸውንና ቤታቸውን ለአዛዉንቶች ፣ ጎረቤቶችና ፣ ዘመዶች ክፍት በማድረግ ፣ ምግብ በመለገስ ፣ ጏደኛ በመሆን ፣ ቤቴ ቤትህ( ቤትሽ) በማለት ሳይሳቀቁ እንደልባቸው በመግባትና በመውጣት የሚአስፈልጋቸውን ሁሉ ሲያደርጉላቸው ነው። ሙላት ፀጋ የአረጋዊያን መረጃ ድርጅት የሃይማኖት ተቋም ባይሆንም ፤ የራዕይአችን ምንጩ የክርስትና እምነታችን ነው። ሌሎችን በማገልገል እናምናለን ፤ በተለይ አረጋዊያንን። ይህን በማድረግ የክርስቶስን ፍቅርና ደግነት ምሳሌ እንከተላለን። አረጋዊያንን መንከባከብ ለኛ ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን መታደልም ነው። ከኛ በፊት የመጡትን በተለያዩ የህይወት ዉጣ ዉረድ በማለፍ ያገለገሉንን ማክበርና "እንወዳችኋለን" በማለት ፍቅራችንንና አድናቆታችንን መግለፅ መንገዳችን ነው።
ድርጅታችን የተሰየመው በሁለት እንቁ ሰዎች ስም ነው። ሙላት "ባባ" ታደሰና ፀጋ "ናነይ" ጣፈጠ ፤ የድርጅቱ መስራቾች አባትና እናት ናቸው። ወላጆቻችን ለኛ የደግነት ምሳሌዎች ናቸው። በአስቸጋሪ ጊዜ እንኳን ያላቸውን ትንሽ ነገር ባባና ናነይ አይጠቀሙም። ከተራቡና ከተረሱት አረጋዊያን ጋር ተካፍለው ሲበሉ እያየን ነው ያደግነው። ደግነታቸው ለይታይነት ሳይሆን የህይወት መንገዳቸው ነበር። ለልጆቻቸውና ለሚአውቋቸው ሁሉ መልካም ምሳሌ ሆነውናል።
መስራቾች ቤኢትዮጲያ ብዙ አዛውንት ለመኖር ሲታገሉ በማየታችን ወላጆቻችን ሲያደርጉት ከነበረው በተሻለ መንገድ ተደራጅተን ለማስቀጠል ጥሪ እንዳለን ተሰማን። ስለዚህ ሙላት ፀጋ የአረጋዊያን መረጃ ድርጅት እውን እንዲሆን አደረግን።
ድርጅታችን ትርፍ የለሽ ድርጅት ብቻ አይደለም ፤ ለኛ ጥሪ ነው። የወላጆቻችንን ህልም ማሟላት ነው። በየቀኑ የምንሰራው ሁሉ የሚመራን ጥሪያችን ነው። በፍቅር ሰዎችን ማገልገል ዋናው አላማችን ነው። በየቀኑ የምንሰራው በመርዳት መንፈስ እየተማርን ነው። አሁን በጎንደር የተጀመረው አንድ ቀን በመላው ኢትዮጲያና በመላው አለም ይስፋፋል የሚል ህልም አለን።


አላማችን
የሙላት ጸጋ የአረጋውያን መርጃ ድርጅት አላማው እርዳታ የሚአስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን አረጋውያንን የፍቅር አገልግሎት መስጠት፤
ክብራቸውን የጠበቀና አክብሮት ያለበት እርዳታ መለገስና "የኔ ነው፤ ቤቴ ነው" ብለው እንዲአስቡ ማድረግ ነው።ለህብረተሰቡ አረጋውያኑ በዘመናቸው ያገለገሉትን፤ አክብሮትና እውቅና በመስጠት አሁን እርዳታ በሚአስፈልጋቸው ጊዜ፤ ጤናቸውን በመንከባከብ፤ የሚአስፈልጋቸውን በመስጠት በቤተሰባችን ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን መልካም ስራ ማስቀጠል ነው።
ራዕይአችን
ራዕይአችን ማንኛውም በእድሜ የገፉ አዣውንት ኢትዮጵያውያን በክብርና በምቾት የእርጅና ዘመናቸውን እንዲኖሩና፤ ሊአገኙ የሚገባውን እርዳታ መስጠት ነው።
አረጋውያንን የሚንከባከብ ህብረተሰብ እንዲፈጠር እናልማለን፤ እንጥራለን።ለአረጋውያኑ የሚአስፈልጋቸውን ሁሉ በማቅረብ፤ ተገቢውን ክብር በመስጠትና፤ የእርጅና ዘመናቸው የደስታ ጉዞ እንዲሆንላቸው ለማድረግ እንጥራለን። ለሌሎች ጥሩ ምሳሌ በመሆን አረጋውያንን የሚአከብር ህብረተሰብ የመገንባት ምኞት አለን።ይህን ራዕይ ያመኑ ሁሉ በመተባበር የአረጋውያንን ደህንነት ለመጠበቅ ቅድሚያ በመስጠት እንዲተባበሩ ጥሪ እናቀርባለን።
ቡድኑን ያግኙ
አሰለፍ ሙላተ
ዳይሬክተር
ሕይወት ሙላት
ረዳት ዳይሬክተር እና ገንዘብ ያዥ

ቤተልሔም ቢኒያም
ጸሐፊ
ማርታ ታደሰ
የቦርድ አባል
ዮሃንስ ጥሩነህ
የቦርድ አባል

ዳንኤል ለገሰ
የቦርድ አባል

የአብ እጅጉ
የቦርድ አባል

ዘመነ ዮሐንስ ትሩነህ
የቦርድ አባል
ተክለወልድ ገሰሰ
የቦርድ አባል
ደስታየሁ ሙላት
የቦርድ አባል
ሂሩት ሙላት
በኢትዮጵያ አስተዳዳሪ
እስክንድር ደረበ
በኢትዮጵያ ረዳት አስተዳዳሪ
ጉዞአችን
በመጀመሪያ...
ገንዘብ ለአባታችን ለአቶ ሙላት ታደሰ በመላክ የደግነት ስራውን እንዲቀጥል እንደግፈው ነበር። ይህን ካለምንም ድርጅት በቤተሰብ ነበር የምናደርገው።
አባታችን አቶ ሙላት ታደሰ ካረፉ በኋላ የሚረዳቸው ሰዎች እንዳይቸገሩ ገንዘብ ለቤተሰብ በመላክ አገልግሎቱ እንዲቀጥል አደረግን።
በአሜሪካ ህጋዊ የሆነ ትርፍ የለሽ ድርጅት ፤ ሙላት ፀጋ የአረጋዊያን መረጃ የተባለውን ድርጅት አቋቋምን። የድርጅቱ መቋቋም ዘላቂ በሆነ መንገድ ችግረኞትን ለመርዳት ችሏል።